ሐምሌ 27/2013 (ዋልታ) – በቻይና ውሃን ግዛት ሁሉም ሰው የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ምርመራ ሊደረግለት ነው።
የግዛቱ አስተዳደር እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የቻለው ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ከፍ ብሎ በመገኘቱ እንደሆነም ተገልጿል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ በግዛቱ የሚኖረው 11 ሚሊዮን ህዝብ ቫይረሱ ከተከሰተበት እ.አ.አ ከ2019 ጀምሮ ክትትል ሲደረግለት ነበር።
ቻይና በአሁኑ ወቅት የቫይረሱ ማገርሸት ምልክተቶች እየታየባት ሲሆን መንግስት ችግሩን ለመከላከል በስፋት ምርመራ ለማካሄድና የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
ባለስልጣናቱ ቫይረሱ ሊስፋፋ የቻለው የዴልታ ዝርያ መከሰትና ወቅቱ የሃገር ውስጥ ቱሪዝም ከፍ የሚልበት ወቅት በመሆኑ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡