በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኬንያ ለሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ሥልጠና ሰጠ

ሰኔ 16/2013 (ዋልታ) – በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከሞራን ካፒታል ማኔጅመንት ጋር በመተባበር በኬንያ ለሚገኙ የዳያስፖራ አባላት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

በሥልጠናው በኬንያ በተለያየ ንግድ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉ ሲሆን፣ ሀብት በማፍራት ጉዳይ ላይ የግማሽ ቀን ሥልጠና ወስደዋል፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር መለስ ዓለም ባደረጉት ንግግር ኤምባሲው በተለያዩ መስኮች ኬንያ ውስጥ ለተሰማሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ኤምባሲው በቅርቡም በኬንያ የስትራትሞር ዩኒቨርሲቲ ለኢትዮጵያውያን የነፃ ትምህርት ዕድል እንዲሰጥ ማስቻሉን አማባሳደር መለስ ጠቁመዋል፡፡