በአዋሽ ቢሾላ የሰራዊት አባላት ምርቃት

በአዋሽ ቢሾላ የሰራዊት አባላት ምርቃት

መስከረም 6/2014 (ዋልታ) የአዋሽ ቢሾላ መሠረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ማዕከል በመሠረታዊ ውትድርና ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመርቋል።

ምሩቃኑ ኢትዮጵያ የገጠማትን የህልውና አደጋ ተከትሎ የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው መሰረታዊ የውትድርና ስልጠናን ያጠናቀቁ የሠራዊት አባላት መሆናቸው ተገልጿል።

ሀገራዊ ግዳጆችን በብቃት በመወጣት ሀገርን ከውስጥ እና ከውጪ ወራሪ ለመጠበቅና ህዝብና ሀገራቸውን በትጋት ለማገልገል በሰንደቅ አላማው ፊት ቃል ገብተዋል።

ኢቢሲ እንደዘገበው በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል።