በአዲስ አበባ ለሚገኙ ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው

ጥቅምት 02/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ተቋማት አመራርና ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

የስልጠናው ዓላማ የባለሙያዎችን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም በጥናትና ምርምር ለማሳደግ ያለመ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ተቋማትን በመገንባት ለከተማዋ ሁለንተናዊ ለውጥ  እንዲያመጡ የሚያስችል እንደሆነም ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር ሀርጋሞ ሀማሞ ተቋሙ ከ2007 ጀምሮ ከ20 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ አመራርና ባለሙያዎች ስልጠና እንደሰጠ ገልጸው፣ ስልጠናው ለባለሙያው የተሻለ አቅም በመገንባት ለህብረተሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ነው ብለዋል።

በሱራፌል መንግስቴ