ሰኔ 19/2013 (ዋልታ) – በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ እጽዋት ማእከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር “አዲስ አበባን እናልብሳት” በሚል እየተካሄደ ነው።
መርሃግብሩን ያስጀመሩት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ በከተማ ደረጃ 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ እንደሚተከል ተናግረዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር አዲስ አበባ ለክልሎች ምሳሌ የሚሆን ሥራ እየሰራች ነው ብለዋል።
እንደ ክልልም 2 ቢሊዮን ችግኝ ለመትከል እየተሰራ መሆኑን አቶ አገኘሁ ተናግረዋል።
መርሀ ግብሩ ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተካሂዷል።
(በምንይሉ ደስይበለው)