በአጋሮ ከተማ እና ጎማ ወረዳ በ123 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

ሰኔ 3/2013 (ዋልታ) – በጅማ ዞን አጋሮ ከተማ እና ጎማ ወረዳ በ123 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመርቀዋል፡፡

በዚህም በአጋሮ ከተማ በ47 ሚሊየን ብር የተገነቡ የከተማ የውስጥ ለውስጥ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ መንገድ፣ የህዝብ መናፈሻ ፓርክ እና የንግድ ማዕከል ፕሮጀክቶች ናቸው የተመረቁት።

የከተማዋ ከንቲባ ነሲብ ያሲን አስተዳደሩ 23 ፕሮጀክቶችን ከአንድ አመት በታች በሆነ ጊዜ በ47 ሚሊየን ብር ወጪ ማጠናቀቅ መቻሉን ገልፀው፣ የነዋሪውን የልማት ጥያቄ የመመለስ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥል ብለዋል።

እንደዚሁም በጎማ ወረዳ ሁለተኛ ትውልድ ጤና ጣቢያ እና የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን ጨምሮ 15 ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል።

የፕሮጀክቶቹ የገንዘብ ወጪ 76 ሚሊየን ብር ሲሆን፣ በፕሮጀክቱ የህዝብ ተሳትፎ ከፍተኛ ነውም ተብሏል።

(በደረሰ አማረ)