በአፋር ክልል በኢንቨስትመንት ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው

 

በአፋር ክልል በኢንቨስትመንት ከተሰማሩ ባለሃብቶች ጋር የአንድ ለአንድ ውይይት የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነሯ ሌሊሴ ነሜ በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የአፋር ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አሲያ ከማል በውይይቱ ተገኝተዋል።

በክልሉ የሚገኘውን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን አስመልክቶ በሚካሄደው ውይይት ላይ በክልሉ መዋእለ ነዋያቸውን ያፈሰሱ ኢንቨስተሮች እና ባለድርሻ አካላትም ተሳታፊ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።