የግብጽ የእስረኞች አያያዝ አሳሳቢ መሆኑን አምንስቲ አስታወቀ

 

የግብጽ ሰብዓዊነት የጎደለው የእስረኞች አያያዝ አሳሳቢ መሆኑን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ፡፡

አምንስቲ ኢንተርናሽናል በዛሬው ዕለት ይፋ ባደረገው ሪፖርቱ የአረብ አብዮት ከተከሰተ ከ10 ዓመት በኋላ የግብጽን የእስረኞች አያያዝ ተችታል፡፡

የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እንዳስታወቁት ከሆነ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊነት በጎደለውና በተጨናነቁ እርስር ቤቶች መታሰራቸውንም ነው የገለጹት፡፡

እስረኞቹ በጨለማ ቤት ውስጥ፣ ንጹህ አየር በማያገኙበት እና ንጽህናቸው ባልተጠበቁ መጸዳጃዎች ውስጥ እንደሚጠቀሙ ነው አምንስቲ የገለጸው፡፡

ይህ ሰብዓዊነት የጎደለው አያያዝም በእስረኞች ላይ አላስፈላጊ ስቃዮች እንዲጋፈጡና አንዳዶቹም ህይወታቸውን እንዳጡ ነው ይፋ ያደረገው፡፡
እስረኞች ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙበት ሁኔታ ያለመኖሩ እንዲሁም ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ወጥነት የሌለው አሰራሮች መንሰራፋታቸውን በሪፖርቱ አትቷል፡፡

በተጨማሪም በእስረኞች ላይ ለ20 ሰዓታት የሚዘልቅ ስቃይ እንደሚደርስባቸውም ተገልጿል፡፡

የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ጥናት ያተኮረው በሀገሪቱ በሚገኙ 16 እስር ቤቶች ውስጥ ነው ተብሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት መረጃን ዋቢ አድርጎ አልጀዚራ እንደዘገበው በግብጽ እስር ቤቶች ውስጥ 114 ሺህ ታራሚዎች ይኖራሉ፡፡