በአፋር ክልል የተገነባው የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች ማቆያ ዛሬ ተመረቀ

የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን በአፋር ክልል ዲቼቶ አካባቢ የተገነባውን የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሽከርካሪዎች መቆያ ተርሚናል ዛሬ ተመረቀ።

ተርሚናሉ በ12 ሂክታር ላይ ያረፈ ሲሆን በአንድ ጊዜ 800 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑ ተገልጿል።

የዲቾቶ የከባድ ተሽከርካሪ ተርሚናል 99 ሚሊየን 279 ሺህ 944 ብር ወጭ ተደረጎበት መገንባቱ ተነግሯል።

(በምንይሉ ደስይበለው)