በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የፕሬስ መግለጫ በጄነቫ ፕሬስ ክለብ ተዘጋጀ

እ.ኤ አ ጃንዋሪ 06 ቀን 2021 የተካሄደው የፕረስ መግለጫ ዋና ዓላማ የህወሃት ቡድን በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ የፈፀመውን ኃላፊነት የጎደለው ተግባር በአገር ህልውና ላይ የደቀነውን አደጋ ለመቀልበስ መንግሥት የህግ የበላይነት ለማስከበር ያደረገው ዘመቻና ከዘመቻውም በኋላ አሁን በተጨባጭ በመሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በትክክል ለማስገንዘብ ነው።

እንደዚሁም በህወሃት ቡድን ጄለዎች የሚናፈሱ የውሸት መረጃዎችን ለማጋለጥ እንደሆነ ተገልጿል።

በፕሬስ መግለጫ ላይ የተሳተፉት በጄነቫ የኢትዮጵያዊያን ኔትወርክ ተወካዮች (አቶ ቅጣው ያየህይራድ)፣ በስዊዘርላንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር አምባሳደር ዘነበ ከበደ፣ የኢትዮጵያ ዋና ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዎስ፣ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳኒኤል በቀለ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢ.ዜ.ማ) ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ናቸው።

በተለይ በፕሬስ መግለጫው ላይ በፓሊናስትነት የተሳተፉት የኢትዮጵያ ዋና ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጥሞቲዎስ፣ የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳኒኤል በቀለ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢ.ዜ.ማ) ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሁኔታው ላይ ያላቸውን ምልከታ አካፍለዋል ከጋዜጠኞችና ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል።

የፕሬስ መግለጫውን በዋነኛነት የመሩት የቀድሞ ኢትዮጵያ አምባሳደር በጄኔቫ ክቡር አምባሳደር ሚኒሊክ ዓለሙ መሆናቸዉን ከዉጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡