የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ. ሩጫ ተጠናቀቀ


መጋቢት 8/2016 (አዲስ ዋልታ) ከ15 ሺሕ ሴቶች በላይ የተሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር ቅድሚያ ለሴቶች የሩጫ ውድድር በጉታኒ ሻንቆ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

በውድድሩ ጉታኒ ሻንቆ በአንደኝነት ስታጠናቅቅ ብርነሽ ደሴ እና መቅደስ ሽመልስ ደግሞ የ2ኛ እና የ3ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቅ ችለዋል፡፡

በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑት በየደረጃው 70 ሺሕ ብር፣ የ45 ሺሕ ብር እንዲሁም የ30 ሺሕ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በውድድሩ ላይ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒሰትር ኤርጌጎ ተስፋዬን (ዶ/ር) ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ አትሌቶች እና አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡

መነሻ እና መድረሻውን አትላስ ሆቴል አካባቢ ያደረገው ውድድሩ “የሴቶችን አቅም እንደግፍ ለውጥን እናፋጥን” በሚል መሪ ሐሳብ ነው የተካሄደው፡፡

በእየሩስ ቀርቁ