በኦሮሚያ ክልል ‘ቡሳ ጎኖፋ’ የተሰኘ ንቅናቄ ተጀመረ

‘ቡሳ ጎኖፋ’ የተሰኘ ንቅናቄ

ግንቦት 17/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል የገዳ ሥርዓት አካልና የኦሮሞ ሕዝብ ጥንታዊ የመረዳጃ ሥርዓት ነው የተባለ ”ቡሳ ጎኖፋ” ንቅናቄ ተጀመረ።

ሥርዓቱ የኦሮሞ ሕዝብ ሰው ሰራሽም ይሁን ተፈጥሯዊ ችግር ሲያጋጥመው ችግሩን ለማለፍ የሚታገዝበት ጥንታዊ ባህል ነው ተብሏል።

ንቅናቄውን ማስጀመር ያስፈለገበት ምክንያትም የሕዝቡን የመረዳዳት ባህል ለማጎልበት እንደሆነና የክልሉ መንግሥት ሥርዓቱ ተቋማዊ መልክ እንዲኖረው ቢሮ ተደራጅቶ እየተመራ መሆኑ ታውቋል።

በንቅናቄው ማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራልና የክልሉ የሥራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW