በኦሮሚያ ክልል 3 ሺሕ 588 የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመተግበር መወሰኑ ተገለፀ

ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር)

የካቲት 4/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንት ቢሮ በተያዘው በጀት ዓመት 3 ሺሕ 588 የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለመተግበር ክልሉ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል፡፡

የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ተሾመ አዱኛ (ዶ/ር) በክልሉ እስካሁን በኢንቨስትመንት አማራጮች ኢኮኖሚን የማሳደግ ተግባር ትኩረት ሳይሰጠው መቆየቱን አንስተው ይህን ተከትሎ የማኅበረሰብን ተጠቃሚነት እንዲሁም የክልሉን ኢኮኖሚ የሚያሳድግ የኢንቨስትመንት አማራጮች ወደ ሥራ ሊገቡ መሆኑን አስታውቀዋል::

በዚህም 534 ሺሕ የሥራ እድል መፍጠር በሚያስችለው የኢንቨስትመንት ሥራም ከ180 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል እንዲሁም 24 ሺሕ ሄክታር መሬት መመደቡን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በክልሉ በግብርናው ዘርፍ ተፈላጊውን ያህል ውጤት ማግኘት ያልተቻለበትን ታሪክ ለመቀየርም በተያዘው የኢንቨስትመንት እቅድ እንድሚሰራ ገልፀው በይበልጥም የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል::

በሄብሮን ዋልታው