በክላስተር የለማ የስንዴ ምርት ጉብኝት ተካሄደ

በክላስተር የለማ የስንዴ ምርት

መጋቢት 28/2014 (ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል ፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ቃሊቲ ወረዳ በክላስተር የለማ የስንዴ ምርት ጉብኝት ተካሄደ፡፡

በክላስተር የለማ የስንዴ ምርቱን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ጌቱ ገመቹን ጨምሮ የክልሉ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም በማሳቸው ላይ የተለያዩ የአትክልት ምርቶችን በማምረት ላይ እንደነበሩ የገለጹት አርሶ አደሮቹ አሁን በስንዴ ልማት የተሻለ ምርትና ዋጋ ማግኘት እንደሚያችላቸው ተናግረዋል፡፡

በሰለሞን በየነ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW