በኮቪድ-19 የሟቾች ቁጥር 3 ሚሊዮን አለፈ

ሚያዚያ 08/2013 (ዋልታ) – በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 3 ሚሊዮን 243 በላይ ደርሷል፡፡

ይሄ ሪፖርት እስከተጠናቀረበት ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ 139 ሚሊየን 716 ሺህ 185  ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል፡፡

ተጨማሪ 118 ሚሊየን 768 ሺህ 975  ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸውን የዎርልድ ኦ ሜትር መረጃ አመላክቷል፡፡

አሜሪካ ከ578 ሺህ 990 በላይ ዜጎቿን በማጣት በቀዳሚነት ስትገኝ ቫይረሱ እየጠነከረባት የሚገኘው ህንድ ከ175 ሺህ 330 በላይ  ሞት በማስመዝገብ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጣለች፡፡

ብራዚል ከ365 ሲህ 950 በላይ ሞት ያስመዘገበች ሲሆኑ ፈረንሳይ እና ሩሲያም ከፍተኛ የሞት መጠን በማስመዘገብ  ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት ተርታ ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል፡፡