«በወጋገን ይቆጥቡ ይሸለሙ» የቁጠባ ማበረታቻ የሎተሪ ዕጣ ወጣ

ሚያዚያ 29/2013 (ዋልታ) – ወጋገን ባንክ ከጥቅምት 1 ቀን እስከ መጋቢት 30 2013 ድረስ «በወጋገን ይቆጥቡ ይሸለሙ» ሲያካሂድ የቆየውን የቁጠባ ማበረታቻ የሎተሪ ዕጣ ሽልማት በብሄራዊ ሎተሪ ወጣ፡፡
የወጋገን ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርቱካን ገብረእግዚ፣ የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራር እንዲሁም የብሄራዊ ሎተሪ ሃላፊዎች በተገኙበት እጣው ወጥቷል፡፡
ባንኩ ዕጣ ያወጣባቸው የሽልማት አይነቶች 1ኛ ዕጣ አንድ የ2019 ሞዴል ዘመናዊ የቤት መኪና፣ 2ኛ ዕጣ ሁለት ባለሶስት ዕግር ተሸከርካሪ፣ 3ኛ ዕጣ 20 የልብስ ማጠቢያ ማሺኖች፣ 4ኛ ዕጣ ባለ 32 ኢንች ኤል ኢዲ ቴሌቪዥኖች እና 5ኛ ዕጣ 40 ስማርት የሞባይል ስልኮች ናቸው፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ብርቱካን ገብረእግዚ ባንኩ በወጋገን ይቆጥቡ ይሸለሙ ያካሄደውን የሎተሪ ዕጣ ሽልማት መርሀ-ግብር ደንበኞች እንዲቆጥቡ የሚያበረታታ ነው ያሉ ሲሆን በአሁን ሰአት ያለው የቁጠባ ባህል የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡
ባንኩ የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች በጋዜጣ ይፋ እንደሚያደርግ እና ለባለ ዕድለኞች እንደሚያስረክብ ተገልጿል፡፡
(በሜሮን መስፍን)