በዓለም ላይ 3.6 ቢሊዮን ሰዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት የላቸውም ተባለ

ኅዳር 21/2015 (ዋልታ) በመላው ዓለም 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ሰዎች የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንደሌላቸው የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።
ለዚህ ደግሞ የከባቢ አየር ለውጥ እና በ2021 የተከሰተው የ’ላ ኒና’ ክስተት ምክንያት ናቸው ተብሏል።
‘ላ ኒና’ በተከሰተባቸው ጊዜያት የምድራችን አብዛኛው ክፍል የወንዞች እና ኩሬዎች መድረቅ ተከስቶ ነበር።
ኤጀንሲው ባወጣው ሪፖርት እንዳስታወቀው በፈረንጆቹ 2050 ይህ ቁጥር ወደ 5 ቢሊየን በላይ ሊያሻቅብ ይችላል።
የሪፖርቱን ይፋ መሆን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የችግሩን አሳሳቢነት ገልፆ ለመፍትሔው መስራት እንደሚገባ አሳስቧል።
ሪፖርቱ የወንዞችን ፍሰት፣ ጎርፍ እና ድርቅን በተመለከተ አሁናዊውን ሁኔታ አመላክቷል ያለው የተባበሩት መንግስታት ይህም በውሃ ክምችት ላይ መስራት የግድ እንደሚል የሚያሳይ ነው ብሏል፡፡