የሰላም ስምምነቱ አዲስ ተስፋ እና ደስታን ፈጥሯል – የፅዮን ማርያም ክብረ በዓል ታዳሚዎች

ኅዳር 21/2015 (ዋልታ) ዓመታዊው የፅዮን ማርያም ክብረ በዓል በርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ፅዮን በድምቀት ተከብሯል።

በክብረ በዓሉ ላይ የአክሱም እንዲሁም የሰሜን ምዕራብ ሀገረ ስብከት ጳጳሳትና በርካታ ምዕመናን ተገኝተው አክብረውታል።

በሀገሪቱ በነበረው ጦርነት ምክንያት ያለፉት የፅዮን ክብረ በዓላት እንደ ከዚህ ቀደሙ ህዝበ ክርስቲያኑ በብዛት ተገኝቶ ባያከብረውም፤ አሁን ላይ የተደረሰው የሰላም ስምምነት አዲስ ተስፋ እና ደስታን የፈጠረ ሆኗል ብለዋል የበዓሉ ተሳታፊዎች።

በሚቀጥለው ዓመት ከአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት በሚሳተፉ የበዓሉ አክባሪዎች እንዲሁም በውጭ ቱሪስቶች ታጅቦ ይከበራል ሲሉ ተስፋቸውን ገልፀዋል ሲል የዘገበው ኢብኮ ነው።