በየም ልዩ ወረዳ በአንድ ጀንበር 1.2 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

ሐምሌ 20/2013 (ዋልታ)፦ በየም ልዩ ወረዳ በአንድ ጀንበር 1ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል መርሐ ግብር በልዩ ወረዳው አሼ ቀበሌ እየተካሄደ ነው።

የልዩ ወረዳው ዋና አፈ ጉባኤ ተናኘ ወንድማገኘው እና ም/አስተዳዳሪና የእርሻና ተፈጥሮ ሀ/ል/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሴይፉ ደምሴን ጨምሮ የልዩ ወረዳው ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የመንግስት ሠራተኞች፣ አርሶአደሮችና የከተማ ነዋሪዎች በመርሐ ግብሩ ላይ ተሳትፈዋል።

ዛሬ በሚካሔደው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም 74 ሽህ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሎም ይጠበቃል።

በልዩ ወረዳው በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 6 ነጥብ 9 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ለማወቅ ተችሏል።
ዘገባው የየም ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዬች ጽ/ቤት ነው::