በጂማ ከተማ ለጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ እና ለመንግስታቸው የድጋፍ ሰልፍ እየተደረገ ነው

የሰልፉ አላማ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ለሰጧቸው ጠንካራ አመራር እና በልማት እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በዲፕሎማሲ ላስመዘገቡት ስኬት ምስጋና ለማቅረብ እና በቀጣይ የከተማዋ ነዋሪዎች ከዶ/ር ዐቢይ ጎን መሆናቸውን ለመግለፅ ያለመ መሆኑን የሰልፉ አዘጋጆች ገልፀዋል፡፡

ሰልፉን ለማድመቅ ከተዘጋጁ ፅሁፎች ውስጥ “ዶ/ር ዐቢይን ለመደገፍ የምንሰስትለት ነፍስም ሆነ ሀብት የለም” የሚሉና ሌሎች ከጠ/ሚ/ሩ ጎን መሆናቸውን የሚገልፁ ፅሁፎችን በመያዝ እና የተለያዩ  መፈክሮችን በማሰማት ወደ ጂማ ሁለገብ ስታዲየም  ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ተገኝተዋል፡፡

በሀይማኖት አባቶች እና አባ ገዳዎች ምርቃት የድጋፍ ሰልፉ የተጀመረ ሲሆን፣ አስራ አንድ አባላት ያሉት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ ለዶ/ር ዐቢይ ይህን የድጋፍ ሰልፍ ማዘጋጀት ያስፈለገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገርን ለማዳን በወሰዱት ቆራጥ አመራር በመደሰት ለማመስገን መሆኑን ገልፀዋል።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አዲሱ ለጋስ እና የጂማ ከተማ ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ናስርን ጨምሮ የተለያዩ የመንግሰት የሰራ ሀላፊዎች  ተገኝተዋልል ፡  ፡

የድጋፍ ሰልፉ በጂማ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን፣ ከ150 ሺህ በላይ ሰዎች በላይ በድጋፍ  በሰልፉ ላይ መገኘታቸውን የድጋፍ ሰልፉ አስተባባሪዎች  ለዋልታ ገልዋል ፡  ፡

(በአለበል አለማየሁ)