ግንቦት 26/2013 (ዋልታ) – በጅማ ዞን ማና ወረዳ የቡ ከተማ በ23 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ የንፁህ መጠጥ ውሃ እና የንግድ ሼድ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
ከዚህ ቀደም የአካባቢው ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ውሃ ለማግኘት ረዥም እርቀት ይጓዙ የነበሩ ሲሆን፣ በዚህም ለከፍተኛ እንግልት ይዳረጉ እንደነበር ገልጸዋል።
በከተማው የተገነባው የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በሶስት አመታት ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ ከ12 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በከተማዋ 16 ኪሎ ሜትር የቤት ለቤት የንፁህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታ መከናወኑና ለንግድ የተገነቡት ሼዶችም መሰራታቸው ተጠቁሟል፡፡
(በደረሰ አማረ)