በጉጂ ዞን መጋዶ ከተማ የእሳት አደጋ ደረሰ

የካቲት 24/2013 (ዋልታ) – በጉጂ ዞን መጋዶ ከተማ ትላንት የተነሳው የእሳት አደጋ ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማውደሙን የኦዶሻኪሶ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዎች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ በዳሶ ታደሰ ገልፀዋል፡፡

በከተማው የተነሳው የእሳት አደጋ 29 መኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን አቃጥሏል ያሉት ሀላፊው በአጠቃላይ አደጋው ወደ 6 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ ብር የሚገመት ንብረት አውድሟል ብለዋል፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ተናረዋል፡፡

በእሳት አደጋው 19 አባወራዎች ንብረታቸው ሙሉ ለሙሉ የወደመባቸው ሲሆን ቤተሰቡን ለመደገፍ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሰራ መሆኑን ኦ.ቢ.ኤን ዘገባ ያሳያል፡፡