338 ኢትዮጵያውያን ከሳውዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ

የካቲት 24/2013 (ዋልታ) – 338 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ከሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቆንስላ ጉዳዮች ዳይረክቶሬት ጄነራል ተወካይ በቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ተገኝተው ለተመላሾቹ አቀባበል ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።