በጌዲዎ እና በምእራብ ጉጂ ዞኖች የተገነቡ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ተመረቁ

 

በጌዲዎ እና በምእራብ ጉጂ ዞኖች የተገነቡ የአገልግሎት መስጫ ተቋማት

በ2010 ዓ.ም በጌዲዎና በምእራብ ጉጂ ዞን አዋሳኝ ወረዳዎች ተከስቶ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው የነበሩ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ግሎባል አሊያንስ ኢትዮጵያ ከዳያስፖራው በተሠበሠበና እና ከዎርልድ ቪዥን ጋር በመተባበር ከ37 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተገነቡ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተመርቀዋል፡፡

ከሁለት አመት በፊት ተከስቶ በነበረው ግጭት በመቶ ሺህዎች ተፈናቅለውና ለችግር ተዳርገው የነበረ ቢሆንም  መንግስት ባፋጣኝ ወደቀያቸው የመመለስና ከተለያዩ አካላት ጋር  የመልሶ ማቋቋም ስራ ሲሰራ ቆይቷል።

በዚህ መሰረት የግሎባል አሊያንስ ኢትዮጵያ የቦርድ አባል ፕሮፌሰር አቻሜለህ ደበላ  ከዲያስፖራ ኢትዮጵያን ባሰበሰበውና ከወርልድ ቪዝን  ጋር በመተባበር ከ37 ሚሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው እያንዳንዳቸው 3ሺህ ሰው ተጠቃሚ የሚያደርጉ አራት የንጹሕ ውሃ  ግንባታዎች  በጌዲዮ ዞን ጌደብ ወረዳ 855  በምእራብ ጉጂ ቀርጫ ወረዳ  855  በጥቅሉ በሁለቱ ዞኖች 1ሺህ 710 የመኖሪያ ቤቶችን ገንብቶ ለማህበረሰቡ አስረክቧል ብለዋል።

እንደ አካባቢው ነዋሪዎች  ገለጻ በግጭቱ ቤት ንብረታቸው ተቃጥሎና ተዘርፎ ችግር ላይ ወድቀው የነበረ ቢሆንም መንግስት ወደቀያቸው እንዲመለሱ ሰላምን በማስፈን መልሶ በማቋቋም ግሎባል አልያንስ ኢትዮጵያና ወርልድ  ቪዝን ደግሞ  ቤት ገንብቶ ከመሰጠት በተጨማሪ  ሁለት በግና 5 ዶሮዎች  ሰጥተውን ማርባት እንዲጀምሩ፣ ንጹህ ውሃ እንዲጠጡ እንዲሁም ምርጥ ዘር በማቅረብ በግብርና እንዲሰማሩ አድርገዋል።

የጎሎባል አልያንስ ኢትዮጵያ ከወርልድ ቪዝን ጋር በጋራ ላለፉት 20 ወራት ሲሰሩት የቆዩት ፕሮጀክቱ ተመላሾችን በማቋቋም፣ የምግብ እርዳታና የሰላም ግንባታ ስራዎችን በመሥራት ተጠናቋል።

(በምንይሉ ደስይበለው)