ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች ቢወጡም የአፈፃፀም ክፍተት እንዳለባቸው ተገለጸ

ፅጌረዳ ዘውዱ

ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችሉ የህግ ማእቀፎች ቢወጡም የአፈፃፀም ክፍተት እንዳለባቸው ተገለጸ።

በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከላከል በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ጋር “ሰላም ለሴቶች፤ ከጓዳ እስከ ሀገር”  በሚል መሪ ሀሳብ ውይይት እየተካሄደ ነው።

በውይይቱ የወጣቶች ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ፅጌረዳ ዘውዱ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ቢኖርም አሁንም የአፈፃፀም ክፍተት እንዳለበት ገልጸዋል።

የህግና የፖሊሲ አፈፃፀም ጉድለትን ለማሳየት ወጣቶችና ሴቶች በሁሉም መልኩ ተሳታፊ መሆን እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።

በዚህም በቀጣይ በተቀናጀ መልኩ ለመስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ከየክልሉ ከተውጣጡ የወጣቶች ፎረም አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል።

በሴቶች ጥቃት ዙሪያ የተሰሩ ስራዎች ተሞክሮም ከክልል የወጣቶች ፎረም አመራሮች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል።

(በትዕግስት ዘላለም)