በግለሰብ መኖሪያ ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲመረት የነበረ የትምባሆ ምርት በቁጥጥር ስር ዋለ

ጥር 3/2014 (ዋልታ) በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በህገ-ወጥ መንገድ ሲመረት የነበረ የትምባሆ ምርት በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ፡፡
የክፍለ ከተማው ምግብ መድኃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደር ቁጥጥር ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ህገ-ወጥ የትምባሆ ምርቱ በቁጥጥር ስር የዋለው በኅብረተሰቡ ጥቆማ ነው፡፡
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ እንጋ እርቃታ እንደተናገሩት የንግድ ፈቃድ የሌለው ግለሰብ የትምባሆ አዋጁንም በጣሰ ሁኔታ ምርት ሲያመርት በኅብረተሰቡ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የክፍለ ከተማው መረጃ ጠቁሟል፡፡
በወንጀሉ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በህግ እንዲጠየቁ የክስ ሂደት ላይ መሆናቸውን የገለፁት ኃላፊው ኅብረተሰቡ እንደ ሁልጊዜው መሰል ሕገወጥ ድርጊቶች ሲያጋጥሙት ለሚመለከተው አካል ጥቆማ እንዲሰጡ ጠይቀው ጽሕፈት ቤቱም የክትትልና ቁጥጥር ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡