በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው

መጋቢት 2/2013 (ዋልታ) – በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል የተመራ ልዑክ በጅቡቲ የስራ ጉብኝት እያደረገ ይገኛል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ጅቡቲ ሲደርስ የጅቡቲ ፖሊስ ኃይል ዳይሬክተር ኮሎኔል አብዱላሂ አብ ፋራህ፣ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም ዲፕሎማቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በሚኖረው ቆይታ በስልጠናና በጠረፍ ደህንነት ዙሪያ ከጅቡቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ይፈራረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከጁቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡