በፓሪስ የኦሎምፒክ ውድድር ለሚሳተፈው ቡድኑ የመለማመጃ ስታዲየም ፈቃድ ስምምነት ተፈረመ

ሕዳር 8/2016 (አዲስ ዋልታ) በፓሪስ የኦሎምፒክ ውድድር ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ቡድን የመለማመጃ ስታዲየም ፈቃድ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ።
ስምምነቱ የተፈረመው በፓሪሱ አንቶኒ ክፍለ ከተማ ከሚገኝ ስታዲየም ጋር ነው።
በሐምሌ ወር ለሚጀምረው የፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር የአትሌቲክስ ቡድኑ ለሚያደርገው ልምምድ የሜዳ ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ እና የአንቶኒ ክፍለ ከተማ ከንቲባ ከንቲባ ዣን-ኢቭ ሶናሌ ናቸው።
በፓሪሱ ኦሎምፒክ በፈረንሳይ እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለቡድኑ አቀባበል ለማድረግ እና በውድድሮች ላይ በመገኘት ቡድኑን ለመደገፍ የሚያስችሉ የዝግጅት ስራዎችን ለመስራትም ከደጋፊ ተወካይች ጋር ውይይት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።