አቶ ኢያሱ ወሰን የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

 የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን  አዲስ ተመራጩ ፕሬዘዳንት ኢያሱ ወሰን

ሕዳር 8/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢያሱ ወሰን የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ ሲካሄድ አቶ ኢያሱ በሙሉ ድምፅ መመረጣቸው ታውቋል።

አቶ ኢያሱ ፕሬዘዳንት ሆነው በተመረጡበት ውድድር የካሜሮኑ ዕጩ በርትራንድ ሜንዱጋ እንዲሁም የሞሮኮ ሞሐመድ ቦድር ተወዳዳሪ እንደነበሩ ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ይህም አቶ ኢያሱ የአፍሪካን ስፖርት በበላይነት በመምራት ከቀድሞ የካፍ ፕሬዚዳንት ይድነቃቸው ተሰማ በመቀጠል ሁለተኛ ኢትዮጵያዊ አድርጓቸዋል።