በ2ኛ ዙር የ40/60 ዕጣ ለወጣላችሁ ባለዕድለኞች ከነገ ጀምሮ ቁልፍ ርክክብ ሊደረግ ነው

የካቲት 28/2013 (ዋልታ) – በሁለተኛ ዙር 40/60 ዕጣ የወጣባቸውን ቤቶች ከነገ ጀምሮ በአፈፃፃማቸው የተሻሉ የግንባታ ሳይቶችን ለባለ ዕድለኞች ቁልፍ ርክክብ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡

ባለእድለኞችም ከነገ ጀምሮ በአፈፃፃማቸው የተሻሉ የግንባታ ሳይቶችን የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በየቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በሚያወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የቤቶቹን ቁልፍ ለባለ ዕድለኞች ርክክብ የሚያደርግ ይሆናል።

በሚወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ቁልፍ የምትረከቡ ባለ ዕድለኞች የቤቶቹን ቀሪ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ማሰራት የምትችሉ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ገልጿል።

በመጀመሪያ ዙር ላይ የተካተቱ 220 ህንፃዎች የሚገኙበት የግንባታ ሳይቶች ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል።

  1. መሪ ሎቄ (14 ህንፃዎች)
  2. እህል ንግድ (5 ህንፃዎች)
  3. ህንፃ አቅሪቢ (8 ህንፃዎች)
  4. አስኮ (13 ህንፃዎች)
  5. አያት 1 ሳይት 1 (14 ህንፃዎች)
  6. አያት 1 ሳይት 2 (38 ህንፃዎች)
  7. አያት 1 ሳይት 3 (41 ህንፃዎች)
  8. አያት 1 ሳይት 4 (39 ህንፃዎች)
  9. ሰሚት (8 ህንፃዎች)
  10. ቦሌ ቡልቡላ ሎት 1 (27 ህንፃዎች)
  11. ቦሌ ቡልቡላ ሎት 2 (13 ህንፃዎች)

መረጃውን ያገኘነው ከአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽ/ቤት ነው፡፡