ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጎርጎራ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን አስጀመሩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

የካቲት 28/2013 (ዋልታ) – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጎርጎራ ገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን በዛሬው ዕለት አስጀመሩ፡፡

በጎርጎራ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን(ዶክተር) ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ ሚኒስትሮች፣ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ተጋባዥ እንግዶች እና ባለሀብቶች ታድመዋል።

በጎርጎራ ‹‹የገበታ ለሀገር›› መርኃ ግብር ከሚለማው ፕሮጀክት ውጭ 134 የሚደርሱ ባለሃብቶች የቦታ ጥያቄ አቅርበዋል ተብሏል።

እያንዳንዳቸው እስከ 500 ሚሊየን ብር የሚደርሱ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎች፣ መዝናኛ ሎጂዎች፣ በግብርና እና ማዕድን ልማት ለመሳተፍ የሚያስችል የኢንቨስትመንት ጥናት ቀርቧል ሲል አብመድ ዘግቧል።