ባለፉት 4 ወራት የዋጋ ግሽበት እየቀነሰ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

ኅዳር 6/2015 (ዋልታ) ባለፉት 4 ወራት የዋጋ ግሽበት በመቀነስ ላይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚው ዘርፍ እያደረገች ያለችውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ እየሰጡ ባለው ማብራሪያ ነው፡፡

የዋጋ ግሽበት የዓለም ሁሉ ፈተና ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ የዋጋ ንረት መነሻ የአቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ምርቶች ወደ ሚፈለጉበት ቦታ በጦርነት ምክንያት እንዳይገቡ መደረጉ ነው ብለዋል፡፡

በዓለም ላይ ያለው ፈተና ለኛ ደግሞ የማክሮ ኢኮኖሚ ስብራት ነው ያሉ ሲሆን ነገር ግን የዋጋ ግሽበቱ ባለፉት 4 ወራት በመቀነስ ላይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ገበያውን ለማረጋጋት የእሁድ ገበያ የራሱን ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ አንስተዋል፡፡

በዙፋን አምባቸው