የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከምስራቅ አፍሪካ የመሪነት ደረጃን መያዙን ጠ/ሚ ዐቢይ ተናገሩ

ኅዳር 6/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከምስራቅ አፍሪካ የመሪነት ደረጃን መያዙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ እየሰጡ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራትም ኢትዮጵያ ግዙፍ ኢኮኖሚ በመገንባ በሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር ሆናለች ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት የሀገሪቱ ኢኮኖሚ 6 ነጥብ 4 በመቶ አጠቃላይ እድገት ማስመዝገቡን ገልፀዋል፡፡

የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በ2014 ዓ.ም መጨረሻ 6 ነጥብ 616 ትሪሊዮን ብር ወይም 126 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

የሀገሪቱ የነብስ ወከፍ ገቢም 1ሺሕ 212 ዶላር መድረሱንም ተናግረዋል፡፡

በ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 7 ነጥብ 5 በመቶ እድገት እንደሚያስመዘግበም ተናግረዋል፡፡