ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 122 የህክምና ዶክተሮችን እያስመረቀ ነው

ግንቦት 21/2013 (ዋልታ) – የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያስተማራቸው 122 የህክምና ዶክተሮች እያስመረቀ ነው፡፡
በምረቃው ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ ዩኒቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን እያፈራ ይገኛል ያሉ ሲሆን ይህም የዩኒቨርሲቲውን ተሞክሮ ያሳያል ነው ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው የማኅበረብ አገልግሎት በመስጠት ይታወቃል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ያደረገው ጥረት አንዱ ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል።
በሥራ ዓለም የተለያዩ ፈተናዎች ያሉ በመሆኑ ተመራቂዎች ከወዲሁ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ እና ቁርጠኛ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።