የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ መዝጊያ ፕሮግራም እያካሄደ ነው

ሰኔ 09/2013 (ዋልታ) – የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ለሁለት ወራት ሲያካሂድ የየቆዬውን የምረጡኝ ቅስቀሳ የመዝጊያ ፕሮግራም በመስቀል አደባባይ እያካሄደ ይገኛል።

በመዝጊያ መርኃግብር ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባልና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ ሀገር ከምርጫ በላይ ነችና ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ በማድረግ ታሪክን ማሻገር ይገባል ብለዋል፡፡

ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተወዳዳሪ ፓርቲዎች የሚደረገው የምረጡኝ ቅስቀሳ ዛሬ ይጠናቀቃል።

(በሳራ ስዩም)