ብልፅግና ፓርቲ መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ድምፅ አገኘ

ሐምሌ 03/2013 (ዋልታ) -በምርጫ 2013 ብልፅግና ፓርቲ መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ድምፅ ማግኘቱን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ካሉት 547 መቀመጫዎች ውስጥ ለ436 ወንበሮች ድምፅ ተሰጥቶ ይፋ በሆነው ውጤት መሰረት ብልፅግና 410ሩን ወንበር አግኝቷል።
አብን 5፣ ኢዜማ 4፣ የግል ተወዳዳሪዎች 4 እንዲሁም የጌዲኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ 2 ወንበር ማግኘታቸውም ተገልጿል።