ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለመራጩ ህዝብ ምስጋና አቀረቡ

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ
ሐምሌ 03/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ነው ምርጫውን ያደረገው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።
የፀጥታ መደፍረስ፣ የኮቪድ 19፣ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ፈታኝ ቢሆንም በተሻለ መፈፀም ተችሏል ብለዋል።
በፈታኝ ሁኔታ የተካሄደው ምርጫ እንደተሟረተበት ሳይሆን በተሻለ አፈፃፀም ተካሂዷል፣ የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ።
ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወን ስላደረጋቸው ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል ፕሬዚዳንቷ፡፡
በተገለፀው ውጤት ላሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ርዕሰ ብሔሯ የተሸነፋችሁ ይህ የመጨረሻ ምርጫ አለመሆኑን ልትገነዘቡ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።