ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት በውጭ የሚኖሩ ወገኖች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆናቸው ተጠቆመ

አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ

ጥቅምት 9/2015 (ዋልታ) የኢትዮጵያን አቋም በማንፀባረቅና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት በውጭ የሚኖሩ ወገኖች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተናገሩ።

በተለያዩ ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከእናት ሀገራቸው ጥቅም ጋር የተቆራኘ አኩሪ እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል ያሉት አምባሳደር ተስፋዬ ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገትና የብልጽግና ጉዞ ድጋፍና እገዛቸውም ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።

በኢንቨስትመንት፣ በክህሎትና በሌሎች የልማት መስኮች ላይ በመሳተፍና ሌሎችም እንዲሳተፉ በማድረግ የነበራቸውን ሚና ጠቅሰው የኢትዮጵያን አቋም በማንፀባረቅና ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ይህንንም አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

በአውሮፓ፣ በአሜሪካና ሌሎች ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም ወዳጆች ለኢትዮጵያ ላበረከቱትና እያበረከቱ ላለው አስተዋጽኦ አምባሳደር ተስፋዬ ምስጋና አቅርበዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!