ቦርዱ የድምፅ መስጫ ቀንን በተመለከተ ሥልጠና እንዲሁም የቁሳቁስ እሸጋ እና ስርጭት እያከናወነ ነው

ግንቦት 30/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ቀንን በተመለከተ ሥልጠና እንዲሁም የቁሳቁስ እሸጋ እና ስርጭት እያከናወነ ይገኛል።

በመጪው ሰኔ 14 ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ የሚገኘው ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ቀንን የተመለከተ ሥልጠና እየሰጠ፣ የድምፅ መስጫ ቁሳቁስ እሸጋ እና ስርጭት እያከናወነ መሆኑን ገልጿል፡፡

ቦርዱ ይህንኑ የቅድመ ዝግጅት እንቅስቃሴውን የሚያስቃኙ ምስሎችን በማህበራዊ ትስስር ገጽ አጋርቷል፡፡