ቪያሪያል የ2020/21 የአውሮፓ ሊግ ሻምፒዮና ሆነ

ግንቦት 19/2013 (ዋልታ) – ቪያሪያል የ2020/21 የአውሮፓ ሊግ ሻምፒዮና ሆኗል።

ቪያሪያል የአውሮፓ ሊግ ሻምፒዮና መሆን የቻለው ማንቺስተር ዩናይትድን በማሸነፍ ነው፡፡

የእንግሊዙ ማንቺስተር ዩናይትድ እና የስፔኑ ቪያሪያልን ያገናኛቸው የሊጉ የመጨረሻ ጫወታ በቪላሪያ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ሞሬኖ በ29ኛው ደቃቃ ላይ ለቪላሪያ፣ ካቫኒ በ55ኛው ደቂቃ ለማንቺስተር ዩናይትድ ባስቆጠሩት ግብ አቻ ተለያይተው በ30 ደቂቃ ተጨማሪ ሰዓት በለመሸናነፋቸው በመለያ ምት 11 ለ 10 ቪያሪያል የአውሮፓ ሊግ ሻምፒዮና መሆኑን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡