ቻይና ኢትዮጵያ በስኬት ያጠናቀቀችውን ምርጫ በተመለከተ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች


ሐምሌ 05/2013 (ዋልታ) –
ኢትዮጵያ በስኬት ያጠናቀቀችውን ምርጫ በተመለከተ ቻይና የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች።
ቻይና በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይዋ ሊያን ዣኦ በኩል ዛሬ ባስተላለፈችው መልዕክት፤ ኢትዮጵያ ያካሄደችውን ምርጫ ስኬታማ በሆነ መልኩ ማጠናቀቋን በመግለጽ በቀጣይ አገራቱ በትብብር ለሁለቱም አገራት ህዝቦች ተጠቃሚነት አብረው እንደሚሰሩ ገልጻለች።
ኢትዮጵያ የቻይና ስትራቴጂክ አጋር መሆኗን የጠቀሱት ቃል አቀባዩ፤ ለቻይና አፍሪካ ትብብርም ኢትዮጵያ ቁልፍ አገር መሆኗን ገልጸዋል።