“ኂሩት አባቷ ማነው?” ፊልም ተመረቀ

ጥር 5/2014 (ዋልታ) ከተሰራ 57 ዓመታትን ያስቆጠረው እና በኢትዮጽያ የመጀመሪያ ፊልም እንደሆነ የሚነገርለት “ኂሩት አባትዋ ማነው?” ፊልም የቴክኖሎጂ እሴት ተጨምሮለት (ዲጂታላይዝድ ተደርጎ) ለምርቃ በቃ።

በ1957 ነሐሴ 21 ቀን ለዕይታ ቀርቦ የነበረ ሲሆን በአገር ዐቀፍ ፊልም እና ማስታወቂያ ድርጅት እንደተዘጋጀም ተነግሯል፡፡

ፊልሙ ባለጥቁርና ነጭ 35 ሚሊ ሜትር ፊልም ሲሆን በአጠቃላይ በወቅቱ ለዝግጅቱ 200 ሺሕ ብር እንደወጣበት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

አሁን እንደ አዲስ እየተመረቀ በሚገኘው ፊልም መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ ዲያስፖራዎች እንዲሁም ሌሎች ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡

የምረቃ መርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡