ጠ/ሚ ዐቢይ ለኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አዲስ ዋና ዳይሬክተር ሾሙ

ጥር 5/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጌታቸው መንግሥቴን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አድርገው ሾሙ።

መንግሥቱ ንጉሤን ደግሞ የባለሥልጣኑ የኤር ናቪጌሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አድርገው መሾማቸውን ከባለሥልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።