አለም አቀፍ የሴቶች ቀን የማጠቃለያ መርሀ ግብር በሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው

መጋቢት 21/2013 (ዋልታ) – ለአንድ ወር በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር የቆየው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን የማጠቃለያ መርሀ ግብር በሰመራ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በዝግጅቱ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ሙና አህመድ ሴቶች በርካታ ችግሮችን እንደሚጋፈጡ ገልፀው፣ በኢኮኖሚው ዘርፍ ውጤታማና ተወዳዳሪ እንዳይሆኑም መስራት እንደሚያስፈልግ አስታውቀዋል፡፡

(በሳራ ስዩም)