የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከ8 አመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን
መጋቢት 21/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ከስምንት አመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ለመመለስ ዛሬ ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል፡፡
ዋልያዎቹ በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ ዛሬ የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ከኮቲዲቯር አቻቸው ጋር ያደርጋሉ፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን የምትወስንበት ወሳኝ ጨዋታ ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ በኮትዲቧር ይደረጋል፡፡
ዋልያዎቹ በጨዋታው ማሸነፍ፣ አቻ መውጣት ወይም ከኒጀር ጋር የምትጫወተው ማዳጋስካር ነጥብ ከጣለች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለካሜሩኑ አፍሪካ ዋንጫ ማለፉን ያረጋግጣል፡፡
ከዚህ ምድብ የኢትዮጵያ ተጋጣሚ አይቮሪኮስት በአምስት ጨዋታ 10 ነጥብ በመያዝ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ስታረጋግጥ ኢትዮጵያ 9 ነጥቦችን ይዛ ትከተላለች፡፡ ማዳጋስካር 7 እንዲሁም ኒጀር 3 ነጥብ ይዘዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኮቲዲቯር ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲዬም ባደረጉት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ዋልያዎቹ 2 ለ 1 ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው፡፡
(በሀብታሙ ገደቤ)