አምስቱ የምስራቅ ኢትዮጵያ አጎራባች ክልሎች በቀጣናው ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ በድሬድዋ ውይይት እያካሄዱ ይገኛሉ

የካቲት 08/2013 (ዋልታ) የአፋር ፣ የሱማሌ ፣ የኦሮሚያ ፣ የሃረሪ ክልሎችና የድሬድዋ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ሃይሎች በአሁናዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታ ላይ ነው በድሬድዋ ከተማ እየመከሩ የሚገኙት ።

የፌደራል ፓሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮምሽነር ጀነራል መላኩ ፈንታ ስብሰባውን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት ፣ በቀጣናው አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮችን ፣ አልሸባብንና ሌሎች ፀረ ሰላም ሃይሎችን ከመቆጣጠር አንፃር ፣ ህገ ወጥ የመሳሪያና የሰዎች ዝውውር እንዲሁም ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ሃይሉ ያለውን ዝግጁነት ይዳሰሳል ብለዋል ፡፡

እንዲሁም አጠቃላይ ከአዳማ እስከ ጅግጅጋ – ጅቡቲ ያለውን እንቅስቃሴ ሰላማዊ ከማድረግ አንፃር እየተከናወኑ ያሉ የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን በተመለከተ ውይይት ይደረጋል ብለዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የፌደራል ፖሊስ ፣ የመከላከያና የክልሎች ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል ባለስልጣናት ተገኝተዋል።
(ምንጭ ፡- የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት )