አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተለያዩ ሀገራት ሚኒስትሮች ጋር ተወያዩ

የካቲት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲልቪ ባይፖ- ተሞን ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
በተመሳሳይ ሚኒስትሩ ከፖርቹጋል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጃኦ ጎሜዝ ክራቪኝዎ ጋር በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
አምባሳደር ታዬ ኢትዮጵያ ከፖርቹጋል ጋር በቱሪዝም፣ በትምህርት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች በትብብር መስራት ትፈልጋለች ሲሉ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል።
የፖርቹጋሉ ሚኒስትር በበኩላቸው አገራቸው የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ትግበራን እንደምትደግፍ ገልፀዋል።