በአሕጉሪቱ ለሚከሰቱ ግጭቶች ፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል – ሙሳፋኪ ማህመት

የካቲት 6/2016 (አዲስ ዋልታ) በአፍሪካ አሕጉር ለሚከሰቱ ግጭቶች ፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳፋኪ ማህመት አሳሰቡ።

44ኛው የአፍሪካ ሕብረት የስራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባን በንግግር የከፈቱት የሕብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳፋኪ የሩስያ ዩክሬን ጦርነት፣ የእስራኤል ፍልስጤም ጦርነት፣ በቀይ ባህር የሚስተዋለው አለመረጋጋት እንዲሁም በአሕጉረ አፍሪካ በሱዳን እና በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለው ግጭት አሕጉሪቱን ዋጋ እያስከፈለ መሆኑን አንስተዋል።

አፍሪካ ከግጭት ነጻ መውጣት አልቻለችም ያሉት ሙሳፋኪ ለግጭቶች ሁሉ የፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።

አፍሪካ የበለጸገችና የምንሻትን አሕጉር እንድትሆን በአንድነት ላይ ትኩረት ማድረግ አለብንም ብለዋል።

በመስከረም ቸርነት