አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጄሪያ የቻይና አምባሳደር ሊ ሊያንሄ ጋር ተወያዩ

በአልጀርያ የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በአልጄሪያ የቻይና አምባሳደር ከሆኑት ሊ ሊያንሄ ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በቻይና አፍሪካ ትብብርና በሌሎች የሁለትዮሽ ትብብር ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው ተብሏል።

አምባሳደሩ በመንግስት በኩል በትግራይ ክልል አስፈላጊ የሆኑ የሰብዓዊ ድጋፍ እና የህክምና ቁሳቁሶችን ለተጎጅዎች ለማድረስ እየተደረገ ስላለው ከፍተኛ ጥረት ገለጻ አድርገውላቸዋል።

በተጨማሪም በሌሎች ቀጠናዊና ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ማድረጋቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።