አምባሳደር ፍፁም አረጋ ከኢጋድ አባል ሀገራት አምባሳደሮች ጋር ተወያዩ

የካቲት 26/2013 (ዋልታ) – በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ በዋሺንግተን ዲሲ ከኢጋድ አባል ሀገራት አምባሳደሮች ጋር በዌቢናር ተወያይተዋል፡፡

በውይይት በጋራ ፍላጎቶች እና ጥቅሞች ላይ ትኩረት ተደርጓል፡፡

አምባሳደ ፍፁም፣ በቀጠናው ችግሮች ሲያጋጥሙ የጋራ መፍትሄ መስጠት እና የጋራ ጥቅሞችን ማስጠበቅ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ትኩረት አድርገው መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡